Fana: At a Speed of Life!

ሰላም እንዲረጋገጥ የሰላም ሰራዊት አባላት ከፍተኛ ሥራ ማከናወናቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ቀጣይነት ያለው ሰላም እንዲረጋገጥ የሰላም ሰራዊት አባላት ያከናወኑት ሥራ ከፍተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

በከተመዋ የተካሄዱ ሐይማኖታዊ እና የአደባባይ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የሰላም ሰራዊት አባላት የእውቅና እና የምስጋና ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግረ÷ የሰላም ሥራ የአመራር ብቻ ሳይሆን የሁሉንም ኅብረተሰብ ተሳትፎ የሚጠይቅ ነው ብለዋል፡፡

እንደ ከተማ ቀጣይነት ያለው ሰላም እንዲረጋገጥ የሰላም ሰራዊት አባላት ያከናወኑት ሥራ ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽ÷ ላከናወኑት ሥራም ምሥጋና አቅርበዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔም በኢትዮጵያዊ ጨዋነት እና እንግዳ ተቀባይነ እንዲከበር ለከተማዋ ነዋሪዎች ጥሪ አቅርበዋል።

የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊድያ ግርማ በበኩላቸው÷ የሰላም ሰራዊት አባላቱ ለመዲናዋ ሰላም መረጋገጥ የላቀ ሚና እንደሚጫወቱ በመጥቀስ ይህንኑ ጥረታቸውንም አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.