Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሁለት ቀናት የሚቀየው የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ዛሬ በአዳማ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ኮሚቴው በሦስት አጀንዳዎች ላይ ውይይት እንደሚያደርግ የተገለጸ ሲሆን÷ የመወያያ ርዕሰ ጉዳዮችንም በአብላጫ ድምፅ በማፅደቅ ስብሰባው እየተካሄደ ነው፡፡

የሊጉ ፕሬዚዳንት አክሊሉ ታደሰ ባደረጉት ንግግር÷ ሊጉ የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማስፋት ስትራቴጂክ ሐሳቦች እና የለውጥ ምኅዋሮች የሚዘወርበት እንዲሆን በርካታ ሥራዎችን መከናወናቸውን አንስተዋል።

በተጠናቀቀው ግማሽ የበጀት ዓመትም በሀገር አቀፍ ደረጃ የወጣቶችን የማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ልኅቀት በተላበሰ ደረጃ ለማሣደግ ተግባራዊ የተደረጉ እንቅስቃሴዎች ውጤታማ ናቸው ብለዋል፡፡

የሊጉ ምክትል ፕሬዚዳንት አባንግ ኩመዳን ባቀረቡት የግማሽ ዓመት ሪፖርት በበጎፈቃድ እንቅስቃሴዎች፣ በንቅናቄ ተግባራት፣ የሚሰጡ ወቅታዊ ተልዕኮዎችን በመፈፀም፣ በሀገራዊ ተልዕኮዎች ወጣቶችን በማስተባበር ረገድ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸው ጠቅሰዋል፡፡

በስብሰባው ለቀጣይ የሥራ አቅጣጫ አቅም መፍጠር የሚችሉ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.