የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ባሕር ዳር ገቡ
አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተ ልዑክ ዛሬ ባሕር ዳር ገብቷል፡፡
የልዑካን ቡድኑም÷ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴን፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበልን፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮችን ያካተተ ነው፡፡
ልዑኩ ባሕር ዳር ሲደርስ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎችም የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል አድርገውላቸዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል፡፡