የድሬዳዋ አሥተዳደር ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ ማካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሁለት ቀናት የሚቆየው የድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት 3ኛ የሥራ ዘመን 3ኛ ዓመት 7ኛ መደበኛ ጉባዔ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በጉባዔው የአስፈጻሚው እና ለምክር ቤቱ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ እንደሚገመገም ተገልጿል፡፡
እንዲሁም የአሥተዳደሩን ሁለንተናዊ የልማትና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎች ለማጠናከር የተዘጋጁ ረቂቅ አዋጆችን ጉባዔው እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል መባሉን የምክር ቤቱ መረጃ አመላክቷል፡፡
በጉባዔው ማጠቃለያም ምክር ቤቱ የተለያዩ ሹመቶችን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!