ስፓርት

መቻል ሲዳማ ቡናን አሸነፈ

By ዮሐንስ ደርበው

February 03, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ13ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ መቻል ሲዳማ ቡናን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

መቻል ማሸነፉን ተከትሎ የሊጉን መሪነት ተረክቧል፡፡

የመቻልን የማሸነፊያ ግቦች ምንይሉ ወንድሙ እና አበባየሁ ዮሐንስ (በራሱ ላይ) ሲያስቆ ጥሩ ለሲዳማ ቡና ቡልቻ ሹራ አስቆጥሯል።

ምሽት 12፡00 ሠዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ አዳማ ከተማ ባሕርዳር ከተማን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የአዳማ ከተማን ጎሎች ዮሴፍ ታረቀኝ እና ቦና ዓሊ ከመረብ ሲያሳርፉ÷ የባሕርዳር ከተማን ብቸኛ ግብ ሀብታሙ ታደሰ አስቆጥሯል።