የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችና አዋጆችን አጸደቀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የድሬዳዋ አስተዳደር 3ኛ የስራ ዘመን 3ኛ ዓመት 7ኛ መደበኛ ጉባዔ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ አዋጆችና ሹመቶች በማፀደቅ ተጠናቀቀ።
በጉባዔው ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ባቀረቡት የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ የአስፈፃሚውንና የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትን የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ጉባኤው ሰፊ ውይይት ካደረገበት በኋላ በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።
ጉባዔው ከአስፈፃሚው ሪፖርት በተጨማሪ የድሬዳዋ አስተዳደር የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በተሻለ ደረጃ ለማቃለል የተዘጋጁ ረቂቅ አዋጆችን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
ከፀደቁት አዋጆች መካከል የድሬዳዋ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች ማሻሻያ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤትን እንደገና ለማቋቋምና የድሬዳዋ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች የዳኞች አስተዳደር ጉባኤን እንደገና ለማቋቋም የወጡ ረቂቅ አዋጆች ተጠቃሽ ናቸው።
መደበኛ ጉባዔው ከረቂቅ አዋጆች በተጨማሪ የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮን በኃላፊነት እንዲመሩ ፅጌረዳ ክፍሌን (ዶ/ር) እና የድሬዳዋ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች የሚመሩ አምስት ዳኞችን በመሾም ጉባኤው መጠናቀቁን ኢዜአ ዘግቧል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!