Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ህዝብን የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የማህበራዊ ተጠቃሚነትን ማሳጣት አይገባም – ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ህዝብን የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የማህበራዊ ተጠቃሚነትን ማሳጣት አይገባም ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የፌዴራል የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ገለጹ፡፡

የፌዴራል ልዑካን ቡድን ከደሴ ከተማና ከደቡብ ወሎ ዞን ከተወጣጡ ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ የምክክር መድረክ አደረገ።

በምክክር መድረኩ ላይ የብልጽግና ፓርቲ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት የፌዴራል የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል፣ የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ፣ የብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሳዳት ነሻ እንዲሁም በአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ፍስሃ ደሳለኝ እና የደሴና የደቡብ ወሎ ዞን አመራሮች ተገኝተዋል።

የፌዴራል የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል በዚህ ወቅት እንዳሉት ፥ የአማራ ህዝብን የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የማህበራዊ ተጠቃሚነትን ማሳጣት አይገባም፡፡

አክለውም ፥ በአማራ ህዝብ ስም መነገድና ያልተገባ ጫና ለመፍጠር የሚደረገዉ ሙከራ ፍፁም ተቀባይነት የለዉም ብለዋል።

የአማራ ህዝብ ሀገር በመገንባትና ኢትዮጵያን በማፅናት ሂደት ላይ የራሱን አበርክቶ በማድረግ ደማቅ አሻራ አሳርፏል፤ ይሄም በደማቅ ታሪክ ላይ ሰፍሮ ይገኛል ሲሉም ነው ገለጹት።

የሀገራችን የሰላም እጦት በርካታ ምክንያቶች አሉት ሲሉ የሚገልጹት ሚኒስትሯ ፥ በተለይም ያልተፈታና የከረመ ችግር፣ አዳዲስ የተፈጠሩ ፍላጎቶችና ዓለም የደረሰበት ደረጃ መድረስ አለመቻላችን ለሀገራችን የሰላም እጦት ዋነኛ ችግሮች ናቸው ብለዋል።

የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ በበኩላቸው ፥ እንደ ከተማ በርካታ አንገብጋቢ የሆኑ የልማት ጥያቄዎችን በቻልነዉ ልክ እየሰራን እንገኛለን ፤ አጠናክረንም እንቀጥላለን፡፡

የብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሳዳት ነሻ ፥ የዴሞክራሲና የፖለቲካ ግንባታ ባህላችንን በማስተካከል ወደ ቀደመዉ ክብራችን መመለስ አለብን ብሎ ብልጽግና ፓርቲ አቋም መያዙን ተናረዋል፡፡

በተደጋጋሚ ጊዜም ከነፍጥ ትግል ወደ ሀሳብ ትግል እንምጣ በሚል ተደጋጋሚ ጥሪ አቅርቧል ሲሉ መግለጻቸውን ከፓርቲው ያገነነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የአማራን ህዝብ ጥያቄዎች ፓርቲያችን ብልጽግና አምኖና ቆጥሮ ይዟል ያሉት ኃላፊው ፥ በከፍተኛ ሁኔታም እንዲፈቱ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ጥያቄዎች ማዕቀፍ ከሌሎች ኢትዮጵያውን ጋር በወንድማማችነትና በእህትማማችነት የትብብር መንፈስ በመሆን እንደሚፈቱም ነው የተናገሩት፡፡

ተፈናቃዮችን ለመመለስ አበረታች ስራ እየተሰራ ነዉ ያሉት አቶ ሳዳት ፥ በቅርቡም በፍጥነት ወደ መኖሪያ ቀያቸው እንደሚመለሱ ጠቁመዋል፡፡

በዚህም በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠውሰው የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቀያቸው ለመመለስ በጋራ ልንሰራ ይገባል ፤ እናንተም ከመንግስት ጎን በመቆም ልታግዙ ይገባል በሚል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.