ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች በተለያዩ ከተሞች እንዲስፋፉ ይሰራል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች እንዲስፋፉ እንደሚሰራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
ከንቲባዋ ይህን ያሉት የጎንደር ከተማ አስተዳደር የምግብ ማዕከል ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ባስቀመጡት ወቅት ነው።
የመሰረት ድንጋዩን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በጋራ አስቀመጠዋል።
ከንቲባዋ በወቅቱ እንደገለጹት፥ አዲስ አበባ እና ጎንደር በተለያዩ ዘርፎች በትብብር በመስራት እህትማማች ከተሞች ናቸው።
በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች እየተሰሩ ነው ያሉት ከንቲባዋ፥ ይህም ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች እንዲስፋፉ መንግስት እየሰራ ነው ብለዋል።
በጎንደር ከተማ የሚገነባው የምግብ ማዕከል ሙሉ በሙሉ እስኪጠናቀቅ የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ሙሉ ወጪውን እንደሚሸፍንም ጠቁመዋል።
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ለፕሮጀክቱ መሳካት የክልሉ መንግስት የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን ጠቅሰዋል።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባዩ አቡሃይ በበኩላቸው እንዳሉት፥ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን በስፋት በማከናወን የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው።
ከአዲስ አበባ ተሞክሮዎችን በማምጣት በከተማዋ የሚገኙ ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍሎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።
በምናለ አየነው
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!