Fana: At a Speed of Life!

የድርቅ አደጋን ለፖለቲካ አላማ ማስፈፀሚያ ለማዋል የሚደረግ ጥረት ተገቢ አይደለም – ኮሚሽኑ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተውን ድርቅ ለፖለቲካ አላማ ማስፈፀሚያ ለማዋል የሚደረግ ጥረት ተገቢ ያልሆነና በፍፁም ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ገለፀ፡፡

የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማርያም(ዶ/ር)÷ አሁን ላይ በሀገሪቱ 6 ነጥብ 6 ሚሊየን ዜጎች የሰብአዊ ድጋፍ የሚሹ መሆኑን ጠቅሰው፤ መንግስት በተቀናጀ መልኩ ለድርቁ ምላሽ ለመስጠት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

ከሰብአዊ ድጋፍ ፍላጎት አንጻር ባለፈው አመት መሸፈን የተቻለው 33 በመቶ ብቻ መሆኑን አስታውሰው፤ መንግስት ባለፉት ስድስት ወራት በ11 ቢሊየን ብር ወጭ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል እህል ገዝቶ ማከፋፈሉን ገልፀዋል።

እርዳታ ሰጭ ተቋማት ያለምንም ማስጠንቀቂያ ድጋፍ መስጠት ማቆማቸውን የገለፁት ኮሚሽነሩ÷ መንግስት ተጨማሪ ሀብት በመመደብ ዜጎቹን መታደግ መቻሉን እና በቀጣይም ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስገንዝበዋል፡፡

በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ እንጂ ረሀብ አለመሆኑን ኮሚሽነሩ ማብራራታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በመሆኑም የተከሰተውን ድርቅ ለፖለቲካ አላማ ማስፈፀሚ ለማዋል የሚደረግ ጥረት ተገቢ ያልሆነና በፍፁም ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አስረድተዋል።

የድርቅ አደጋውን ተከትሎ የፌደራል መግስት የሰብአዊ ድጋፍና ፈጣን ምላሽ እየሰጠ መሆኑን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ ÷ በዚህ ረገድ የክልሎች ተሳትፎ ሊጠናከር ይገባል ብለዋል።

በመንግስት እየተደረጉ ያሉ ድጋፎች በትክክል ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች መድረሱን የማረጋገጥ ስራ በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባም አሳስበዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.