Fana: At a Speed of Life!

በዲጂታል የነዳጅ ግብይት ሥርዓት ከ155 ቢሊየን ብር በላይ ግብይት ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዲጂታል የነዳጅ ግብይት ሥርዓት ከ155 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ግብይት መከናወኑን የነዳጂና ኢነርጅ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

የነዳጅ ግብይት በዲጂታል ሥርዓት መካሄድ ከጀመረበት ሚያዝያ 2015 ጀምሮ እስካሁን ከ155 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ግብይት መፈጸሙን የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር በቀለች ኩማ ተናግረዋል፡፡

ግብይቱ በዲጅታል መሆኑ በዘርፉ ያለውን ኮንትሮባንድ በመቆጣጠር፣ የነዳጅ ብክነትን በማስቀረት እና ግብይቱን በማቀላጠፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱንም ጠቅሰዋል፡፡

ይሁን እንጂ አሁንም በግብይት ሂደቱ ላይ ክፍተቶች መኖራቸውን ነው ያመላከቱት፡፡

ግብይታቸውን በዲጅታል የማይፈጽሙ ማደያዎችን በመከታተልና ኦዲት በማድረግ ከነዳጅ ትስስሩ እንዲወጡ አቅጣጫ ተቀምጧል ብለዋል፡፡

በሀገሪቱ ከሚገኙ 1 ሺህ 589 ማደያዎች መካከልም 1 ሺህ 469 ያህሉ ግብይታቸውን በቴሌ ብር እየፈጸሙ መሆናቸውንም ነው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የተናገሩት፡፡

በመሳፍንት እያዩ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.