Fana: At a Speed of Life!

ቴይለር ስዊፍት ለ4ኛ ጊዜ የግራሚ አዋርድ ሽልማትን አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካዊቷ አቀንቃኝ ቴይለር ስዊፍት የ2024 የዓመቱ ምርጥ አልበም ሽልማትን አሸንፋለች፡፡

ቴይለር ስዊፍት የዓመቱ ምርጥ አልበም ሽልማትን ስታሸንፍ ይህ ለ4ኛ ጊዜ ነው።

በዚህም ቴይለር ስዊፍት ሶሰት ጊዜ የምርጥ አልበም ሽልማት ያሸነፉትን ስቴቪ ዎንደር፣ ፖል ሳይመን እና ፍራንክ ሲናትራ የተባሉ ድምፃውያንን በመብልጥ በግራሚ አዋርድ ታሪክ ስሟን በቀዳሚነት አስፍራለች፡፡

አሜሪካዊት አቀንቃኝ እንድታሸነፍ ያደረጋት በ2022 የተለቀቀው “ሚድ ናይትስ” የተባለው አልበሟ ሲሆን በአድናቂዎቿ ዘንድ ከፍተኛ ዝናን አትርፎላት እንደነበር ተመላክቷል፡፡

ሚሌይ ሳይረስ እና ቤሊ አይሊሽ ሁለተኛ እና ሶሰተኛ ደረጃን በመያዝ ሽልማታቸውን ከዝነኛዋ ድምፃዊ ሴሊን ዲዮን እጅ ተቀብለዋል፡፡

በሴቶች የዓመቱ ምርጥ ዘፍን ዘርፍ ቤሊ አይሊሽ “ዋት ወዝ ኤ ሜድ ፎር” በተሰኘው ዘፈኗ ስታሸነፍ፤ የዓመቱ አዲስ አርቲስት ሽልማትን ደግሞ ቪክቶሪያ ሞኔት አሸንፋለች፡፡

በወንዶች የግራሚ አዋርድ ታሪክ ኪለር ማይክ በቀዳሚነት ስሙ የሚነሳ የራፕ አርቲስት ሲሆን ሶስት ጊዜ የግራሚ አዋርድ ሽልማትን ማሸነፉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.