Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን ለዜጎቿ ምቹ ለማድረግ በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን ለአሁኑም ይሁን ለቀጣዩ ትውልድ የተመቸች ሀገር ማድረግ የሚያስችሉ የልማትና ግንባታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አይተናል ሲሉ ወደ ሀገር ቤት የገቡ ሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን ገለጹ፡፡

በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚኖሩ ሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን ከታኅሣስ 20 ቀን 2016 እስከ መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም በሦስት ዙር ወደ ሀገር ቤት እንዲመጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው።

ሀገራዊ ጥሪውን ተከትሎም በመጀመሪያው ዙር ወደ ሀገር ቤት የመጡ ሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን የተለያዩ አካባቢዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በተመለከቷቸው ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎችና የቱሪስት መስኅቦች መደሰታቸውንም ነው ለኢዜአ የተናገሩት፡፡

በኢትዮጵያ ለትውልድ የሚጠቅሙ ዘመን ተሻጋሪ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ተመልክተናል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያን ለአሁኑም ይሁን ለቀጣዩ ትውልድ የተመቸች ሀገር ማድረግ የሚያስችሉ አስደናቂ የልማትና ግንባታ ሥራዎች በስፋት እየተከናወኑ መሆኑንም ጎብኝተናል ነው ያሉት፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.