የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ነገ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ማብራሪያ ይሰጣሉ

By ዮሐንስ ደርበው

February 05, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነገ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ከ2፡30 ጀምሮ እንደሚካሄድ የምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ያዕቆብ ወልደሰማያት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በስብሰባውም በምክር ቤቱ አሠራርና የአባላት ሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 መሠረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች በቃል ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ገልጸዋል፡፡