ቢዝነስ

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል

By ዮሐንስ ደርበው

February 05, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር ሲሸጥ በነበረበት ዋጋ የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ከጥር 28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በሥራ ላይ በነበረበት ዋጋ እንዲቀጥል መወሰኑ ተገልጿል፡፡