Fana: At a Speed of Life!

ለአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ታዳሚዎች አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ተሳታፊዎች የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ እናትዓለም መለስ እንዳሉት÷ በከተማዋ የሚገኙ ሆቴሎች እንደ ሁልጊዜው ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት አድርገዋል፡፡

በከተማዋ አዳዲስና ነባር የመዝናኛ መዳረሻዎችና ፓርኮችም እንግዶችን እየጠበቁ ነው ብለዋል።

በጤና አገልግሎት በኩልም የሕክምና ዝግጅት መደረጉን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም እንግዶች በቆይታቸው ለሚያከናውኑት ግብይት የገበያ ማዕከላት ከዘመናዊ አገልግሎት ጋር ዝግጁ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ የካቲት 9 እና 10 ቀን 2016 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን÷ 44ኛው የአባል ሀገራቱ የሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ የካቲት 6 እና 7 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.