Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ሠላምና ፀጥታን በተመለከተ ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፡-

👉 በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፍላጎት የማሳኪያ ስልት (ልምምድ) ችግር አለበት፤ በዚህም ከውይይት ይልቅ ጠመንጃ ማንሳትን ያስቀደመ መሆኑ ትክክል አለመሆኑን አንስተዋል፡፡

👉 በጦርነት የሚገኝ ጥቅም የለም፤ ጥቅም ያለው ከሠላም ነው፤ ይህን ሁልጊዜም መገንዘብና መኖር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

👉 ከሸኔ ጋር የተካሄደው ድርድር ለሕዝብ ይፋ የማናደርገው የተጨበጠ ጉዳይ ስለሌለ ነው ይፋ ያልተደረገው፤ በቀጣይ ተጨባጭ ጉዳይ ሲኖር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይፋ ይደረጋል፡፡

👉 ከሽምቅ ተዋጊ ጋር ድርድር ማድረግ በኢትዮጵያ አልተጀመረም፤ በዓለም ላይ በተለያዩ ሀገራት የሚተገበር ነው ብለዋል፡፡

👉 የራስን ሕዝብ እየበደሉ እታገልልሃለሁ ማለት ተገቢ አይደለም፤ ልቦና ገዝቶ ወደ ውይይትና ሠላም መምጣት እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

👉 ኢትዮጵያ ውስጥ በምርጫ እና በዴሞክራሲ ካልሆነ በአፈሙዝ ስልጣን ይዞ ማሥተዳደር እንደማይቻልም በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.