Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ሕብረት ጉባዔ ስኬታማ እንዲሆን ዝግጅት መደረጉ ተመላካተ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 37ኛው የአፍሪካ ሕብረት ጉባዔ የተሳካ እንዲሆን የዝግጅት ሥራዎች መከናወናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በሰጡት መግለጫ÷ ብሔራዊ ኮሚቴ ተዋቅሮ ለሦስት ወራት በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡

ለዘንድሮው የሕብረቱ ጉባዔ ካለፈው ዓመት በተለየ መልኩ ከ35 ተቋማት ጋር በመሆን የቅድመ ዝግጅት ሥራ በቅንጅት መሠራቱን አስታውቀዋል፡፡

እንግዶች በሚኖራቸው ቆይታ ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችሉ ሥራዎች መሠራታቸውንም አመላክተዋል፡፡

ጉባዔውን ለመዘገብም በመቶዎች የሚቆጠሩ የውጭ ሀገርና የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን መመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡

በቅድስት ብርሃኑ እና መሳፍንት እያዩ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.