Fana: At a Speed of Life!

በጄኔራል አበባው ታደሠ የተመራ ልዑክ በዓለም አቀፍ የመከላከያ ትዕይንት ላይ ተሳተፈ

 

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሠ የተመራው ልዑክ በሳዑዲ ዓረቢያ ተዘጋጅቶ ለዕይታ በቀረበው ዓለም አቀፍ የመከላከያ ትዕይንት ላይ ተሳተፈ።

በሳዑዲ ዓረቢያ መከላከያ ሚኒስቴር የወታደራዊ አታሼ አስተዳደር አስተባባሪነት ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ105 ባላይ ለሚሆኑ ሀገራት ልዑካን ቡድን እና ለጎብኝዎች ክፍት ሆኖ የቆየው አለም አቀፍ የመከላከያ ትዕይንት ተጠናቋል።

ትዕይንቱ በሁለት ቀናት ቆይታው የነገው የዓለም ሀገራት መከላከያ ዝግጅት እና ትጥቅ ምን ሊመስል እንደሚችል ያመላከተ መሆኑን መገንዘብ መቻሉን ከመከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ቀጣይ አለም ላይ ሊኖሩ የሚችሉ የመከላከያ ትጥቆች ከነፍስ ወከፍ ትጥቅ ጀምሮ፣ የግንኙነት መሳሪያና ሁሉ አቀፍ የተናጠል እና የቡድን ትጥቆች ከዘመኑ ጋር አብረው የሚራመዱ ስለመሆናቸውም ትዕይንቱ አመላካች መሆኑ ተገልጿል፡፡

እንዲሁም ሳዑዲ ዓረቢያ በ2030 ተግባራዊ ለማድረግ ከያዘችው ራዕይ አንጸር 50በመቶ የመከላከያ ምርቷን በሀገር ዉስጥ የማምረት ውጥኗን የማሳካት ጉዞዋ ተስፋ ሰጪ መሆኑ የተመላከተበት ትዕይንት መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ጄኔራል አበባው ታደሠ እና ልዑካቸው በሳዑዲ አረቢያ ቆይታቸው የሳዑዲ የካዴት ትምህርት ቤትን ፣የወታደራዊ አልባሳት አምራች ኩባንያን ፣ የኢንዱስትሪ የምርምር ማዕከላትን የተመለከቱ ሲሆን÷ ድርጅቶች ሁኔታዎች ከተመቻቹ ከኢትዮጵያ ጋር አብረው የመሥራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል።

በጄኔራል አበባው የተመራ አራት አባላት ያሉት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ልዑካን ቡድን መክፈቻዉን ጨምሮ ትዕይንቱን በመታደም ቆይታውን አጠናቆ ተመልሷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.