Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል 5 ነጥብ 3 ሚሊየን ተማሪዎች የምገባ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በአሁኑ ወቅት 5 ነጥብ 3 ሚሊየን ተማሪዎች የትምህርት ቤት ምገባ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

በቢሮው የእቅድና በጀት ዝግጅት ዳይሬክተር ሃሰን እንድሪስ እንዳሉት፥ በጀት ዓመቱ ከቅድመ መደበኛ እስከ 2ኛ ደረጃ ትምህርት 11 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች በትምህር ገበታ ላይ ይገኛሉ፡፡

ተማሪዎች በተለያዩ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ምክንያቶች ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ አስፈላጊው ክትትል እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዚህ ረገድ በሕብረተሰቡ ተሳተፎ እና በመንንግስት ድጎማ የሚቀርበው የትምህር ቤት ምገባ አገልግሎት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ነው የገለጹት፡፡

በአሁኑ ወቅትም በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች 5 ነጥብ 3 ሚሊየን ተማሪዎች የት/ቤት ምገባ አገልግሎት ተጠቃሚ እንደሆኑ አቶ ሃሰን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስረድተዋል፡፡

የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች በአርብቶ አደር አካባቢዎች ከቅድመ መደበኛ እስከ 8ኛ ክፍል እና በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ ከቅድመ መደበኛ እስከ 4ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.