Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ባህል ግንባታ ዘርፍ አፈጻጸሙን እየገመገመ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ባህል ግንባታ ዘርፍ በስድስት ወራት ውስጥ የነበረውን የስራ አፈጻጸም እየገመገመ ነው።

በመድረኩ የሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደር የፓርቲው ተወካዮች፣ የዘርፉን አፈጻጸም ሪፖርት የሚያቀርቡ ሲሆን በዚህ ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ውይይቶች ይካሄዳሉም ተብሏል።

በኢትዮጵያ ለሚስተዋሉ የዴሞክራሲ ልምምድ ስብራቶች መፍትሄ ለማበጀትም በውይይቱ ይመከራል ተብሏል።

በመድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፖለቲካ ባህል ግንባታ ዘርፍ አስተባባሪ መለሰ ዓለሙ÷ የተጀመሩ የዴሞክራሲያዊ ልምምዶች ውጤታማ እንዲሆኑ ሁሉም አካል ተሳታፊ እንዲሆን ስራዎች ተጀምረዋል ብለዋል።

የዴሞክራሲ ባህልን ለማዳበር የሲቪክ ማህበረሰብን አቅም ማሳደግ፣ የሴቶችና የወጣቶችን ተሳትፎ በማሳደግ በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማጉላት መስራት ላይም ትኩረት መሰጠቱን አመልክተዋል።

በይስማው አደራው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.