Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከኮሞሮስ ዩኒየን ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኮሞሮስ ዩኒየን ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የኮሞሮስ ዩኒየን ፕሬዚዳንትን እና የልዑካን ቡድናቸውን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በይፋዊ የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት ተቀብለዋል።

በውይይታቸውም÷ የጋራ የዕድገት ርዕይ፣ ትብብር እና መከባበርን አስመልክተው በትኩረት መምከራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ በአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበርነታቸው ያሳዩትን ምሳሌነት ያለው አመራር አድንቀዋል፡፡

ከዚህ አንፃር በእርሳቸው አመራር ኅብረቱ ወደ ቡድን 20 መግባት የቻለበትን እርምጃ አውስተዋል፡፡

ሁለቱ መሪዎች የጋራ ጥረት በፈተናዎች እና መፃዒ ዕድሎችን በመጠቀም ብሎም በመተለም ላይ ያለውን አስፈላጊነት በመቀበል ወደፊት ተመልካች በሆነ መንገድ በቀጣናዊና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.