Fana: At a Speed of Life!

የአፋር ክልል ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶችን ለአዲስ አበባ ከተማ አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ከተለያዩ ወረዳዎች የተሰበሰቡ ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶችን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስረክቧል፡፡

ቅርሶቹን የአፋር ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ አሕመድ አብዱቃድር ለአስተዳደሩ አስረክበዋል።

ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶች በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚዬም የሚደራጁ ቅርሶችን በማሰባሰብ እንዲደራጅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባቀረበው ጥሪ መሰረት ነው ቅርሶቹ የተበረከቱት፡፡

በከተማ አስተዳድሩ የከንቲባ ጽ/ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቁ÷ የአፋር ክልል ከተለያዩ ወረዳዎች ያሰባሰባቸውን ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶችን በማበርከቱ ምስጋና አቅርዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.