Fana: At a Speed of Life!

የተሰጥኦ ማበልፀጊያ ት/ቤት ሀብት ፈጣሪ ወጣቶችን የምናፈራበት ነው – በለጠ ሞላ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተሰጥኦ ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት ሀብት ፈጣሪ የሆኑ ወጣቶችን በሀገራችን የምናፈራበት ነው ሲሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተሰጥኦ ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት ከዓለም አቀፍ የወጣቶች ህብረት እና የዘፍጥረት ብክለት ቅነሳና ችሎታ ልማት ኩባንያ ጋር አብሮ ለመስራት የሚስችል የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር)፥ የብዙዎች አጋርነት ለብዙዎች ውጤታማነት ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በትብብር ላይ ትኩረት በማድረግ እንሰራለን ብለዋል፡፡

ወጣቶች ከራሳቸው አልፈው ሀገር እንዲረዱ ማስቻያ ከሆኑ ተቋማት አንዱ የተሰጥኦ ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት እንደሆነም ነው የገለጹት፡፡

በዚህም ሚኒስትሩ አጋር ተቋማትን እያስተባበረ ትልቅ ውጤት ለማምጣት መሰራት አለበት ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የአይ አይ ኤፍ በኢትዮጵያ ሊቀመንበር ኪም ጃህዩብ በበኩላቸው፥ ከሰላምና ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር እየሰሩ መሆኑን እንደተናገሩ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህም ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተሰጥኦ ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት ጋር በሰው ሀብት ልማት፣ በማይንድ ሴት፣ በፈጠራ እና በዲጂታላይዜሽንና ሀገር ወዳድ እንዲሆኑም ጭምር እንደሚሰሩም ነው የተናገሩት፡፡

ጂፒ-ቲዲሲ ሀገር በቀል ድርጅት መስራች የሆኑት ፋንታሁን አበበ (ዶ/ር)፥ ድርጅታቸው ከትምህርት ቤቱ ጋር ይፋዊ አጋር ሆኖ በገንዘብና በዓይነት ከማህበራዊ ኃላፊነት ፈንድ፣ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን እንደሚሰሩ አንስተዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.