አቶ ማሞ ምህረቱ ከቪዛ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ከቪዛ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሪያን ማኪነርኒ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ ኢትዮጵያ ከቪዛ ኩባንያ ጋር ያላትን አጋርነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
አዳዲስ የዲጂታል ክፍያ አማራጮችን ማስፋፋት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውንም የባንኩ መረጃ ያመላክታል፡፡