Fana: At a Speed of Life!

“ስራ በክህሎት ይመራል” በሚል መሪ ሀሳብ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “ስራ በክህሎት ይመራል” በሚል መሪ ሀሳብ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከክልልና ተጠሪ ተቋማት ጋር የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው።

የበጀት አመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት የእቅድ የአፈፃፀም ግምገማ እና የምክክር መድረክ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በአፋር ክልል ሰመራ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በመድረኩ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የ’እንኳን ደህና መጣችሁ’ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ንጉሱ ጥላሁን÷ በመድረኩ የተጠሪ ተቋማት የየክልሉ የስራ አፈፃፀም እና የቀጣይ እቅድ ላይ ውይይት ይደረጋል ብለዋል፡፡

ያጋጠሙ ድሎችና ተግዳሮቶች ለውይይት ይቀርባሉ፤ ይህም ጠንካራውን ለማስቀጠል ክፍተቶችን ለማረም ይረዳልም ነው ያሉት።

መድረኩ እስከ የካቲት 2 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡

በፈቲያ አብደላ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.