Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ አንቶኒዮ ጉተሬዝን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራትና ተቋማት መሪዎች ይሳተፋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራትና ተቋማት መሪዎች እንደሚሳተፉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ÷ በ37ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ 34 የአፍሪካ ሀገራት፣ የዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ድርጅት መሪዎች እንደሚሳተፉ ተናግረዋል፡፡

በሚቀጥሉት ቀናት የሚሳተፉ ሀገራት እና ተቋማት ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡

በጉባዔው የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ፣ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) እና የዓረብ ሊግ መሪዎችን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራትና ተቋማት መሪዎች እንደሚታደሙ ጠቅሰዋል፡፡

በፍሬሕይወት ሰፊው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.