የወጣቶችና አፍላ ወጣቶችን የጤና አጠባበቅ ሥርዓት ለማሻሻል የሚያግዝ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የወጣቶችና አፍላ ወጣቶች የጤና አጠባበቅ ሥርዓትን ለማሻሻል ያግዛል የተባለ ብሄራዊ ፕሮጀክት ይፋ ተደርጓል።
ፕሮጀክቱ ለሶስት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን÷በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ጋምቤላ እና ሶማሌ ክልሎች ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።
ፕሮጀክቱ ተስማሚ የጤና አገልግሎት መፍጠር ላይ ትኩረት አድርገው የሚሰሩ የወጣት ማህበራትና አባላትን ቁጥር መጨመር፣ የህብረተሰቡን ጤናን ማሻሻልና ተሳትፏቸውን ማሳደግ ላይ በትብብር እንደሚሰራ ተመላክቷል፡፡
በተለይም በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች የሚገኙ ወጣቶችንና አፍላ ወጣቶችን ይበልጥ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ነው የተጠቆመው፡፡
ፕሮጀክቱን ጤና ሚኒስቴር ከፓዝፋይንደር ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የሚያከናውኑት መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
በመራኦል ከድር