አምባሳደር ምስጋኑ ከኢንዶኔዢያ አምባሳደር፣ ከየመን ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚ እና ከኒውዚላንድ አምባሳደር ጋር መከሩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የኢንዶኔዢያ አምባሳደር ቡሲራ ባንሱር፣ ከየመን ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚ አምባሳደር ያህያ አል ኤሪያኒ እና ከኒውዚላንድ አምባሳደር ሚካኤል አፕቶን ጋር ተወያይተዋል፡፡
ውይይታቸውም በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡
አምባሳደር አል ቡሲራ ባንሱር፥ ኢትዮጵያና ኢንዶኔዢያ ያላቸውን ግንኙነት በማድነቅ፥ በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለይም በንግድ፣ ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት ላይ በርካታ የትብብር ዘርፎች መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡
አምባሳደር ያህያ አል ኤሪያኒ በበኩላቸው የኢትዮ-የመን ግንኙነት የሚበረታታ እንደሆነ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አክለውም፥ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ የመናውያን ለሚደረገው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አመስግነዋል።
በተጨማሪም አምባሳደሩ በኢትዮጵያ የኒውዚላንድ አምባሳደር ከሆኑት ሚካኤል አፕቶን ጋር የተወያዩ ሲሆን ÷ በሁለቱ ሀገራትመካከል በግብርና ምርታማነት፣ በታዳሽ ሃይል ልማትና የአየር ንብረት ለውጥን በመዋጋት ረገድ የኢንቨስትመንትና የአቅም ግንባታ ትብብርን ማሳደግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ÷ ሀገራቱ በልማትና በሰብአዊ ድጋፍያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ሊያጠናክሩ ይገባል ነው ያሉት።
አምባሳደር ሚካኤል አፕቶን በበኩላቸው ÷ ኒውዚላንድ በኢነርጂ፣ በግብርና ፣ በአቅም ግንባታ ፣ በልማት እና በሰብዓዊ ድጋፍ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር የምትሰራውን ስራ ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል፡፡
ሁለቱ ወገኖች በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የጋራ ጠቀሜታ ባላቸው ጉዳዮች ላይም መክረዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!