Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል ከነገ ጀምሮ የስራ ሰዓት ለውጥ ይደረጋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የሙቀት መጠን እየጨመረ በመምጣቱ የመንግስት የስራ ሰዓት ላይ ከነገ ጀምሮ ለውጥ እንደሚደረግ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት አስታወቀ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፒተር ሆው እንደገለጹት÷ በክልሉ የሙቀቱ መጨመር ለስራ ምቹ ባለመሆኑ ከየካቲት 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ወራት የሚቆይ የስራ ሰዓት ለውጥ ይደረጋል።

በዚሁ መሰረትም ቀደም ሲል የመደበኛው የስራ ሰዓት ከጠዋቱ አንድ ሰዓት እስከ ስድስት ሰዓት ተኩል የነበረው ከአንድ ሰዓት እስከ አምስት ሰዓት ተኩል እንደሚሆን አስታውቀዋል።

እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከዘጠኝ ሰዓት እስከ አስራ አንድ ተኩል የነበረው ከአስር ሰዓት እስከ አስራ ሁለት ሰዓት ተኩል እንዲሆን መወሰኑን ገልጸዋል።

የስራ ሰዓት ለውጡ በማጃንግ ዞን የመንገሽና የጎደሬ ወረዳዎችን እንደማይጨምር መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በተደረገው የሰዓት ማስተካከያ መሰረትም የክልሉ የመንግስት ሰራተኞች በተጠቀሰው የስራ ስዓት በተቋማቸው በመገኘት ሥራቸውን እንዲያከናውኑ አሳስበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.