Fana: At a Speed of Life!

9ኛውን የከተሞች ፎረም ለማስተናገድ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከየካቲት 9 እስከ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ የሚካሄደውን 9ኛው ሀገር አቀፍ የከተሞች ፎረም ለማስተናገድ ዝግጅት ማድረጉን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አስታወቀ፡፡

እንግዶችን ለማስተናገድ ኮሚቴ ተቋቁሞ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ሰናይት ሰለሞን ተናግረዋል፡፡

ለአብነትም የእንግዶች ማረፊያ እንዲሁም የፎረሙ ተሳታፊ ከተሞች የሚተዋወቁበት የዐውደ-ርዕይ ቦታ መዘጋጀቱን ጠቅሰዋል፡፡

የክልሉ ሕዝብ በኢትዮጵያዊነት ባህል እንግዶችን ለመቀበል ዝግጅት አድርጓል ማለታቸውን የወላይታ ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በፎረሙ ከ200 የሚልቁ ከተሞችና የተለያዩ ተቋማት ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.