የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ሞተር አልባ ትራንስፖርት ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

By Tibebu Kebede

June 03, 2020

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሞተር አልባ ትራንስፖርት ስትራቴጂን የትራስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ይፋ አድርገዋል።

ስትራቴጂው የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ለማሻሻልና ሁሉን አቀፍ ልማትን ለማረጋገጥ ሀገሪቱ በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ውስጥ የምትተገብራቸውን እርምጃዎች በዝርዝር ያስቀመጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡