በጅማ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
መድረኩ “ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በውይይት መድረኩ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፣ የብልጽግና ፓርቲ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከሕብረተሰቡ ጋር እየመከሩ ነው፡፡
መድረኩ የሕብረተሰቡን መሠረታዊ ጥያቄዎች ተረድቶ ለመፍታት ከማገዙም በላይ ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትንና ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር እንደሚረዳ ተጠቁሟል።