Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል የተፋሰስ ልማት ሥራ ተጀመረ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል የበጋ የተፋሰስ ልማትና የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ ተጀምሯል።

የበጋ የተፋሰስ ልማትና የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራው በክልሉ በሚገኙ ሶስት የገጠር ወረዳዎች በተመረጡ 10 ተፋሰሶች ላይ ነው በዘመቻ የተጀመረው።

የሐረሪ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ልማት ቢሮ ሃላፊ ሮዛ ዑመር ÷ በክልሉ ከዚህ በፊት በተከናወነ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ የከርሰ ምድር ውሃ መጠንን ከማሳደጉ ባለፈ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር አስችሏል ብለዋል።

የዘንድሮው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ በ2 ሺህ 200 ሄክታር መሬት ላይ የሚከናወን ሲሆን ÷በዚህም ከ30 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች እንደሚሳተፉ ተመላክቷል፡፡

የተፋሰስ ልማት ሥራው ለአንድ ወር እንደሚካሄድም ተጠቁሟል፡፡

በተሾመ ኃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.