የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን 992 ሚሊየን ብር ገቢ አገኘ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ባለፉት ስድስት ወራት ከ992 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡
ገቢው ከማምረቻ ሼዶች በለማ መሬት ኪራይ፣ ለመኖሪያ ቤቶች ከሚያገለግሉ አፓርትመንቶች እና ከህንጻዎች ኪራይ ነው የተገኘው፡፡
ኮርፖሬሽኑ በግማሽ ዓመቱ ከ244 ሚሊየን ብር በላይ ትርፍ ማግኘቱንም የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡