Fana: At a Speed of Life!

በወላይታ ሶዶ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ2 ሰዎች ሕይወት አለፈ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ሶዶ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ23 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡

አደጋው ዛሬ ከጠዋቱ 2 ሰዓት 30 ላይ ከባድ የጭነት ተሳቢ ተሽከርካሪ ከሕዝብ ማመላለሻ፣ ከፒካፕ ተሽከርካሪ፣ ከባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) እና ከሞተር ሳይክል ጋር በመጋጨቱ ነው የደረሰው፡፡

በዚህም የሁለት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ23 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን የሶዶ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ተስፋዬ ምስጋናው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች የሕክምና እርዳታ እየተደረላቸው ሲሆን÷የአደጋው መንስዔም እየተጣራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በማስተዋል አሰፋ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.