Fana: At a Speed of Life!

የህዝብ ውግንና ያለው ለውጥን የሚመራ አመራር ሊፈጠር እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ውግንና ያለውና ለውጥን የሚመራ አመራር ሊፈጠር እንደሚገባ የአጋሮ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

“ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላም እና ሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ በአጋሮ ከተማ ህዝባዊ ውይይት ተካሂዷል።

በመድረኩ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ወጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር ) እንደገለጹት÷ የጽንፈኝነት አስተሳሰብ አሁን ላለችው ኢትዮጵያ ፈተና እንደሆነ ገልፀዋል።

የአጋሮ ከተማ ከንቲባ ነዚፍ መሐመዳሚን በበኩላቸው ÷ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት የተረጋገጠባት ሀገርን ለመገንባት ሁሉም ዜጋ ሀላፊነቱን መወጣት አለበት ብለዋል።

የህዝብ ውግንና ያለው ለውጥን የሚመራ አመራር ማፍራት እንደሚገባም በውይይቱ ተሳታፊዎች ተነስቷል።

የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ፍትሓዊነት የጎደለው የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም የዋጋ ንረት የዜጎችን የእለት ተእለት ህይወት እየፈተነ እንደሚገኝም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።

ከቡና ግብይት ጋር ተያይዞ ያለው አሻጥር መፈታት እንዳለበትም ነዋሪዎቹ ጠቁሙዋል።

በሌላ በኩል አሸባሪው ሸኔ መንግስት ያመቻቸውን የሰላም አማራጭ ተጠቅሞ ትጥቁን መፍታትና ወደ ማህብረሰቡ መቀላቀል እንዳለበትም ነዋሪዎች አመላክተዋል፡፡

የአካባቢን ሰላም በመጠብቅ ረገድም ህብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር መስራት እንዳለበት በመድረኩ ተጠቁሟል፡፡

በውይይት መድረኩ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ወጌሶ (ዶ/ር ኢ/ር ) በተጨማሪ የጋምቤላ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ታኩይ ጆክ እና ሌሎች የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

በወርቅአፈራው ያለው

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_televisionበመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.