Fana: At a Speed of Life!

ኮርፖሬሽኑ ለውኃ ማከሚያ የሚያገለግል ኬሚካል በሀገር ውስጥ ማምረት ጀመረ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለውኃ ማከሚያ የሚያገለግል ኬሚካል በሀገር ውስጥ ማምረት ጀመረ፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አሰፈፃሚ ኢንጂነር ሁንዴሳ ደሳለኝ (ዶ/ር) እንደገለጹት÷ ኮርፖሬሽኑ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በዘርፉ ውጤታማ ሥራዎችን እያከናወነ ነው።

በተለይም ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካትና እሴት ጨምሮ አገልግሎት ላይ ለማዋል እያደረገ ያለው ጥረት አዎንታዊ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል።

ከዚህ ውስጥም ለሚያመርተው የውኃ ማከሚያ ኬሚካል በውጭ ምንዛሪ የሚገባውን የአልሙኒየም ሃይድሮ ኦክሳይድ በሀገር ውስጥ ምርት መተካት መቻሉን ጠቁመዋል።

ኮርፖሬሽኑ በአሁኑ ወቅት የጎማ ምርቶች ለመተካት እየሰራ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

አሁኑ ላይ በሀገሪቱ 3 ሺህ 700 ሄክታር መሬት ላይ የጎማ ዛፋ ምርት መኖሩን ጠቅሰው÷ በዘርፉ ከውጭ የሚገባውን ምርት ለመተካትና የማቀነባበሪያ ፋብሪካዎችን ለመክፈት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

የስንዴ ምርት ዋግ ወይም በሽታን ለመከላከል የሚያስችል ፀረ- አረም ኬሚካል ሙሉ ለሙሉ በሀገር ውስጥ ለመተካትም እየተሰራ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ከዚህ ውስጥ አምስት አይነት ኬሚካሎችን በጥናት ደረጃ የተለዩ ሲሆን÷ ለዚሁ ስኬትም ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ኮርፖሬሽኑ ባለፉት ስድስት ወራት 2 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ገቢ ማገኘቱንም ዋና ሥራ አሰፈፃሚው አመላክተዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.