Fana: At a Speed of Life!

በሚቀጥሉት 10 ቀናት ለዝናብ መፈጠር አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ሁኔታዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ – ኢንስቲትዩቱ

አዲስ አበባ፣የካቲት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሚቀጥሉት 10 ቀናት ለዝናብ መፈጠር አስተዋጽኦ ሊያደርጉ የሚችሉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ከዕለት ወደ ዕለት እንደሚጠናከሩ የኢትዮጵያ ሚትዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡

በዚህ መሰረትም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ የመካከለኛው ኢትዮጵያና የምሥራቅ አማራ እንዲሁም የስምጥ ሸለቆ አጎራባች አካባቢዎች ዝናብ ማግኘት እንደሚጀምሩ ተጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ምዕራብ እንዲሁም በስምጥ ሸለቆና አጎራባች አካባቢዎች የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡

በመሆኑም በመጀመሪያዎቹ አምስት ቀናት ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የኢንስቲትዩቱ መረጃ ያስረዳል፡፡

በተጨማሪም አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች በአንዳንድ ቦታዎቻቸው ላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ተጠቅሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.