የዓድዋ ድል መታሰቢያ ከነገ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት ይሆናል
አዲስ አበባ፣የካቲት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ፒያሳ አካባቢ የተገነባው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ከነገ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆን ተገለጸ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዳስታወቁት÷የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ከነገ ጀምሮ በሚወጣው መርሐ ግብር መሰረት ለጎብኚዎች ክፍት ይሆናል።
“የዓድዋ ድል፤ መታሰቢያውም የሁላችንም ነው፤ ኑ ቤታችሁን እና ታሪካችሁን ጎብኙ።” ሲሉም ከንቲባዋ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በትናንትናው እለት ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወቃል፡፡