Fana: At a Speed of Life!

የሰኔ ወር የነዳጅ ምርት መሸጫ ባለበት   እንደሚቀጥል ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ግንቦት 27፣ 2012 (ኤፍ. ቢ.ሲ ) የሰኔ ወር የአውሮፕላን ነዳጅ ጨምሮ የሌሎች የነዳጅ ምርቶች  መሸጫ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል።

መንግስት የሀገሪቱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥል ለማስቻል አሁን በስራ ላይ ያለው የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ.ም  ባለበት  እንዲቀጥል መወሰኑ ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ አያይዞም በዓለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊያደርግ የሚችል መሆኑን አስታውቋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.