Fana: At a Speed of Life!

18 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ያስመዘገቡ 129 የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መሳብ መቻሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ 18 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ያስመዘገቡ 129 የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትና 29 ቢሊየን ብር ያስመዘገቡ 292 የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መዉሰዳቸው ተገለጸ።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀሙን እየገመገመ ነው።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በወቅቱ ባደረጉት ንግግር፥ አዳዲስ ኢንቨስትመንት ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የታለመለትን ግብ ማሳካት በሚያስችል መልኩ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ነው ያነሱት።

የዘርፉን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የፋይናንስ፣ የመሬት እና የግብዓት ውስንነቶችን መቅረፍ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በንቅናቄው ከ6 ነጥብ 7 ሚሊየን ቶን ግብዓት ለጨርቃ ጨርቅ፣ ኬሚካል እና ምግብ አምራቾች መቅረቡም ነው የተገለጸው።

በዚህ የግማሽ ዓመት ለከፍተኛ አምራቾች 23 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር እና ለአነስተኛና መካከለኛ አምራቾች 3 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ብድር መቅረቡ በመድረኩ ተነስቷል።

እንዲሁም ለአምራቾች 274 ሚሊየን ዶላር መቅረቡን እና 994 ሚሊየን ዶላር በተኪ ምርት ስትራቴጂ ማዳን መቻሉም ነው የተጠቆመው።

እንዲሁም ምርቶችን ወደ ውጭ ከላኩ ድርጅቶች 140 ሚሊየን ዶላር መገኘቱም ተነግሯል።

በኤፍሬም ምትኩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.