Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ሥራ ተገብቷል- ግብረ-ኃይሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 37ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 44ኛው የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ዝግጅት አድርጎ ወደ ሥራ መግባቱን አስታወቀ፡፡

ግብረ-ኃይሉ ባወጣው መግለጫ÷ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከናወኑ የፀጥታ ሥራዎች ስኬታማ መሆናቸውን ገልጿል፡፡

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔም በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ ኃይል አሰማርቶ በቴክኖሎጂ የታገዘ የፀጥታና የደኅንነት ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ የተቀናጀ ኦፕሬሽን እንዲሁም የሕብረተሰቡ ተሳትፎ ለመዲናዋ አስተማማኝ ሰላም መሆን ከፍኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ተጠቅሷል፡፡

አዲስ አበባ የአፍሪካ ኅብረት እና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ በመሆኗ÷ ሰላማዊ ሆና እንድትቀጥል ግብረ-ኃይሉ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ እንደሚገኝ ተነስቷል፡፡

በኢትዮጵያዊ ባህል እንግዶችን በማስተናገድ እና በየትኛውም እቅንስቃሴያቸው ተባባሪ በመሆን ሕዝቡ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ግብረ-ኃይሉ ጥሪ አቅርቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.