በመዲናዋ ከየካቲት 8 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር አይቻልም
አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ከየካቲት 8 ቀን ጠዋት 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም ጠዋት 2 ሰዓት ድረስ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር መከልከሉን የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
ክልከላው የጸጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን እንደማያካትት ነው የተገለጸው፡፡
ስለሆነም የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶች እና አሽከርካሪዎች እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ተጠይቋል፡፡
የተቀመጠውን ክልከላ በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡
#Ethiopia #AddisAbeba
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!