በተለያዩ 20 ከተሞች ነገ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በነገው ዕለት በተለያዩ 20 ከተሞች ሕዝባዊ የውይይት መድረክ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
መድረኩ “ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና”በሚል መሪ ሃሳብ ነው የሚካሄደው፡፡
በሕዝባዊ ውይይቱ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከነዋሪዎች ጋር እንደሚመክሩ ተጠቁሟል፡፡
ለዚህም ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ውይይት ወደ ሚካሄድባቸው ከተሞች እየገቡ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡