Fana: At a Speed of Life!

ነገ ለሚካሄደው ሕዝባዊ ውይይት ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ድሬዳዋ ገቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ነገ በድሬዳዋ ከተማ ለሚካሄደው ሕዝባዊ ውይይት ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ወደ ከተማዋ ገብተዋል።

በነገው ዕለት “ኅብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና”በሚል መሪ ሐሳብ በ20 ከተሞች ሕዝባዊ ውይይቶች ይካሄዳሉ፡፡

በድሬዳዋ ከተማ የሚካሄደውን ሕዝባዊ ውይይት ለመምራትም የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እና በብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጸጋዬ ማሞ ወደ ከተማዋ ገብተዋል፡፡

አመራሮቹ ድሬዳዋ ሲገቡ የአሥተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጁሃርን ጨምሮ የከተማዋ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በይስማው አደራው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.