Fana: At a Speed of Life!

ከነገ ጀምሮ የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እስከሚጠናቀቅ ለተሸከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከነገ ጀምሮ 37ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 44ኛው የህብረቱ አስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሸከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡

ጉባዔው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከታች የተገለጹት መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ አሽከርካሪዎችም አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

• ከፓርላማ መብራት-በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር – መስቀል አደባባይ ፍላሚንጎ – ኦምሎፒያ – ወሎ ሰፈር – ጃፓን ኤምባሲ -ፍሬንድ ሺፕ -ቦሌ ቀለበት መንገድ -ኤርፖርት፣

• ከፓርላማ መብራት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር -በብሔራዊ ቤተ – መንግስት -በፍልውሃ – በብሔራዊ ቴአትር- ሜክሲኮ አደባባይ – አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ዙሪያ፣

• ከፓርላማ መብራት -ብሔራዊ ቤተ-መንግስት – ወዳጅነት ፓርክ – ንግድ ማተሚያ ቤት – ሞናርክ ሆቴል-ቴዎድሮስ አደባባይ-ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል- ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን- ብሔራዊ ቴአትር -ሜክሲኮ አደባባይ፣

• ከፓርላማ መብራት-በሸራተን ሆቴል ቁልቁለቱን-ፍልውሃና አምባሳደር ቴአትር ዙሪያውን፣

• ከንግድ ምክር ቤት ጀምሮ በሱዳን ኤምባሲ-አፍሪካ ህብረት ዋናው በር-ሳርቤት ድረስ በሁለቱም አቅጣጫዎች፣

ከሐሙስ የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እንግዶች እስከሚመለሱ ድረስ ግራና ቀኝ በሁለቱም አቅጣጫ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ ነው ተብሏል፡፡

የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ይሁን መረጃ ለመስጠት በስልክ ቁጥር 011-1-11-01-11፣ 011-5-52-63-03 ፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 ፣ 011-5-54-36-81 እንዲሁም 987፣ 991 እና 916 ነፃ የስልክ መስመሮችን መጠቀም እንደሚቻል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ጉባዔውን በሰላምና በስኬት ለማጠናቀቅ እንዲቻል በሚከናወነው የፀጥታ ሥራ እና የትራፊክ ፍሰቱ የተሳለጠ እንዲሆን አሽከርካሪዎች ሌሎች ተለዋጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ተጠይቀዋል፡፡

ኅብረተሰቡም እንደሁልጊዜው ለፀጥታ አካላት ሥራ ተባባሪ እዲሆን ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.