አቶ አወሉ አብዲና መለስ ዓለሙ ጅግጅጋ ገቡ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በነገው ዕለት “ኅብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሐሳብ በ20 ከተሞች ሕዝባዊ ውይይቶች ይካሄዳሉ፡፡
በሶማሌ ክልል የሚካሄደውን ሕዝባዊ ውይይት ለመምራትም የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር አወሉ አብዲ እና የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካ ባህል ግንባታ ዘርፍ አስተባባሪ መለስ አለሙ ጅግጅጋ ገብተዋል፡፡
አመራሮቹ ጅግጅጋ ከተማ ገራድ ዊልዋል አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሶማሌ ክልል አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
በክልሉ ጅግጅጋ፣ ደገሀቡር፣ ቀብሪዳሀርና ጎዴ ከተሞች ሕዝባዊ የውይይት መድረኮች እንደሚካሄዱ ተገልጿል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!