አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች ቀብሪደሃር ገቡ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች በሶማሌ ክልል ነገ የሚካሄደውን ሕዝባዊ ውይይት ለመምራት ቀብሪደሃር ገብተዋል፡፡
አመራሮቹ ቀብሪደሃር ሲደርሱ የክልልና የዞን አመራሮች እንዲሁም የአካባቢው ማኅበረሰብ አቀባበል አድርጎላቸዋል፡፡
በክልሉ ጅግጅጋ፣ ደገሀቡር፣ ቀብሪዳሀርና ጎዴ ከተሞች ሕዝባዊ የውይይት መድረኮች እንደሚካሄዱ ተገልጿል፡፡
በነገው ዕለት “ኅብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሐሳብ በ20 ከተሞች ሕዝባዊ ውይይቶች ይካሄዳሉ፡፡
ሕዝባዊ ውይይቱ የተጀመሩ ሁለንተናዊ ሀገራዊ የድል ጉዞ ለማጠናከር እና ተግዳሮቶችን በውይይትና በትብብር ለመፍታት የላቀ ሚና እንደሚኖረው ተመላክቷል፡፡