የኢትዮ-ቱርክ የኢንቨስትመንትና የንግድ ፎረም ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ-ቱርክ የኢንቨስትመንትና የንግድ ፎረም በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡
በፎረሙ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የስራ ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አባላት፣ የቱሪክ የንግዱ ማህበረሰብ አባላትና ሌሎችም ተሳትፈዋል፡፡
በፎረሙ በኢትዮጵያ እና በቱርክ መካከል ያለውን የንግድ እና የኢኮኖሚ ትብብር ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር መደረጉን በኢትዮጵያ የቱርክ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር በርክ ባራን በዚህ ወቅት ÷ ፎረሙ ኢትዮጵያ እና ቱርክ በንግድና ኢኮኖሚው ዘርፍ ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር የላቀ ፋይዳ አለው ብለዋል።