ሩሲያ ለ4 ዓመት ከሁሉም ስፖርታዊ ውድድሮች ታገደች
አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሩሲያ ለ4 ዓመት በሁሉም ስፖርታዊ ውድድርች እንዳትሳተፍ ማገዱን የዓለም አቀፍ ፀረ አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ(ዋዳ) አስታውቋል።
የዋዳ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በስዊዘር ላንድ ባካሄደው ስብሰባ ነው ሩሲያ ለአራት ዓመታት በማንኛውም ስፓርታዊ ውድድር እንዳትሳተፍ ውሳኔ ያስተላለፈው።
ኮሚቴው ውሳኔውን ያሳለፈውም በሀገሪቱ በሚስተዋለው የአበረታች ንጥረ ነገር ቅሌት ጋር በተያያዘ መሆኑ ነው የተገለጸው።
በውሳኔው መሰረትም ሩሲያ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር 2020 ላይ በሚካሄደው የቶኪዮ ኦሎምፒክም ሆነ በ2022 ኳታር በሚካሄደው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታ ላይ አትሳተፍም።
በአንፃሩ ከአበረታች ንጥረ ነገሮች ነፃ መሆናቸውን ማረጋገጥ የሚችሉ የሀገሪቱ አትሌቶች ገለልተኛ በሆነ ሰንደቅ ዓላማ መወዳደር የሚችሉ መሆኑ ተመላክቷል።